D.r Eyob Mamo

D.r Eyob Mamo Ethiopian prosperity
make ur life easier ..... read more
always be happy n think posstive

ትችሉ ነበር አሁንም ትችላላችሁ!አንዳንድ ሰዎች የእሳቤ ሂደት ይህንን ይመስላል፡-“እንደምችል አውቀዋለሁ” በሚል ጠንካራ እሳቤ ይጀምሩና ከዚያም ቀስ በቀስ፣ “የምችል ይመስለኛል” ወደሚል እሳ...
17/12/2022

ትችሉ ነበር አሁንም ትችላላችሁ!

አንዳንድ ሰዎች የእሳቤ ሂደት ይህንን ይመስላል፡-

“እንደምችል አውቀዋለሁ” በሚል ጠንካራ እሳቤ ይጀምሩና ከዚያም ቀስ በቀስ፣ “የምችል ይመስለኛል” ወደሚል እሳቤ ወረድ ይላሉ፡፡ ብዙም ሳይቆዩ፣ “የምችል ይመስለኝ ነበር” ወደሚለው እሳቤ ከተንሻራተቱ በኋላ በመጨረሻ “አልችል” በማለት ይደመድሙታል፡፡

አንባቢዎቼ!!! ይህ ለብዙዎች ውድቀት ምክንያት የሆነ የእሳቤ ሂደት ለእናነተ አልተፈቀደላችሁም፡፡

እንደምንችል እናውቀው ነበር! እንችል ነበር! አሁንም እንችላለን!

Dr-Eyob-Mamo

ጠንከር በሉ!“አንዳንድ ጊዜ አንድን ግንዛቤ ለማግኘት መጎዳት ይኖርብሃል፣ ለማደግ መውደቅ ይኖርብሃል፣ ለማግኘት ማጣት ይኖርብሃል፣ ምክንያቱም የህይወትን ትልልቅ ትምህርቶች የምትማረው በህመም...
17/12/2022

ጠንከር በሉ!

“አንዳንድ ጊዜ አንድን ግንዛቤ ለማግኘት መጎዳት ይኖርብሃል፣ ለማደግ መውደቅ ይኖርብሃል፣ ለማግኘት ማጣት ይኖርብሃል፣ ምክንያቱም የህይወትን ትልልቅ ትምህርቶች የምትማረው በህመም ልምምድ ውስጥ ስለሆነ ነው” (Alicia Taylor)፡፡

“ማንም ሰው እንዲነካኝና እንዲጎዳኝ አልፈልግም . . . ምንም ነገር እንዲሆንብኝ አልፈልግም . . . አንድም ስህተት መስራት አልፈልግም . . . ምንም ነገር ማጣት አልፈልግም . . . ምንም አይነት ህመም አልፈልግም . . .”

ከላይ የተጠቀሱትና መሰል እሳቤዎችና አባባሎች ደስ የማለታቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከእውነታው እጅጉን የራቁ እንደሆኑ ግን ጥርጥር የለውም፡፡ ማንኛውንም ትርጉም ያለውንና መጨረሻው ያማረ ነገር ለማግኘት፣ ልምምዱን ተከትሎ የሚመጣውን ህመምና ጉዳት መታገስ የግድ ነው፡፡

• እውነታ አንድ፡- ሳንጎዳና ደስ የማይል ስሜት በሚሰጠን ልምምድ ውስጥ ሳናልፍ ምንም አይነት ትርጉም ያለው ሕይወትና እድገት ማግኘት አንችልም፡፡

• እውነታ ሁለት፡- ለእድገትና ለስኬታማነት ብንሰራም ሆነ ባንሰራም ጉዳትን ማስተናገዳችን አይቀርም፡፡ ስለሆነም፣ ባለንበት ቆመን ወይም ወደ ኋላ እየተንሸራተትን ከምንጎዳ ወደ ፊት እየተራመድን፣ እያደግንና ሕይወትን እየኖርናት ብንጎዳ የተመረጠ ነው፡፡

ከተጎዱ አይቀር እየተማሩ፣ እያደጉ፣ እየተሻሻሉና ሕይወትን እያጣጣሙ መጎዳት! እንዴት ደስ የሚልና ሙሉ የሆነ ሕይወት!

Dr-Eyob-Mamo

አንባቢ ነኝ!• በራእዬ እና በምከታተለው ዓማዬ ዙሪያ ዘወትር አነባለሁ!• የእኔን፣ የቤተሰቤን፣ የንግዴን፣ የመስሪያ ቤቴንና የሃገሬን ሁኔታ በሚያሻሽል ርእስ ዙሪያ ዘወትር አነባለሁ!• ያነበ...
15/12/2022

አንባቢ ነኝ!

• በራእዬ እና በምከታተለው ዓማዬ ዙሪያ ዘወትር አነባለሁ!

• የእኔን፣ የቤተሰቤን፣ የንግዴን፣ የመስሪያ ቤቴንና የሃገሬን ሁኔታ በሚያሻሽል ርእስ ዙሪያ ዘወትር አነባለሁ!

• ያነበብኩት ወደ ተግባር ለመለወጥ የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ!

• ለውጥ ጊዜ እንደሚፈልግ ስለማውቅ የጀመርኩትን የለውጥ መንገድ በቀላሉ የማቆም ሰው አይደለሁም!

• አነባለሁ! አድጋለሁ! እለወጣለሁ! ከራሴ አልፌ ለሌላው እተርፋለሁ!

ዛሬ አንድ ጠቃሚ ነገር ይነበብ!

መልካም እሁድ!

Dr-Eyob-Mamo

የኳታር ዓለም ዋንጫ ድምቀት የሆነው ጋኒም አል-ሙፍታህ ***************** ጋኒም አል-ሙፍታህ ይባላል፤ የ20 ዓመት ዕድሜ ያለው ይህ የኳታር ዜጋ፣ Caudal Regression Syn...
21/11/2022

የኳታር ዓለም ዋንጫ ድምቀት የሆነው ጋኒም አል-ሙፍታህ
*****************

ጋኒም አል-ሙፍታህ ይባላል፤ የ20 ዓመት ዕድሜ ያለው ይህ የኳታር ዜጋ፣ Caudal Regression Syndrome (CDS) በተባለ ችግር ምክንያት ከወገብ በታች አካል የለውም።

እናቱ ከመወለዱ በፊት ልጇ ችግሩ እንዳለበት ተነግሯት በበርካቶች "ልጅሽን አስወርጂ" በሚል ብትመከርም፣ እናት ግን ጋኒምን ወልዳ ችግሩን አብራ መጋፈጥን መርጣለች።

ከአባቱ ጋር በመሆንም "ልጃችን ከወገቡ በታች አካል ባይኖረውም አንዳችን ቀኝ እግር፣ ሌላችን ግራ እግር እንሆንለታለን” ሲሉ ቃል በመግባት የዓለምን ፈተና አብረውት ለመታገል ቆረጡ።

የሚጋባ ፈገግታ የተቸረው ጋኒም በማኅበራዊ ሚዲያው ለሚሊዮኖች ንቃትን የሚፈጥር ወጣት ሆኗል።

ቀድሞ በጓደኞቹ ማንጓጠጥ ሊያቋርጠው የነበረውን ትምህርት ቀጥሎም በፖለቲካል ሳይንስ ዲግሪውን ለማግኘት እየተማረ ይገኛል።

ዛሬ ደግሞ የ2022ቱ የኳታር የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ድምቀት ሆኖ አሳልፏል።

ግብ አውጡ እንጂ!“አማካኝ ተሰጥኦ፣ አማካኝ ምኞት እና አማካኝ የትምህርት ደረጃ ያለው ሰው ግራና ቀኝ የማይልና ያተኮረ ግብን ይዞ ከተከተለ በሕብረተሰቡ መካከለ ከሚገኝ አለ የተባለ አስደናቂ...
16/11/2022

ግብ አውጡ እንጂ!

“አማካኝ ተሰጥኦ፣ አማካኝ ምኞት እና አማካኝ የትምህርት ደረጃ ያለው ሰው ግራና ቀኝ የማይልና ያተኮረ ግብን ይዞ ከተከተለ በሕብረተሰቡ መካከለ ከሚገኝ አለ የተባለ አስደናቂና ሊቅ ከሆነ ሰው አልፎና ልቆ ሊገኝ ይችላል” – Mary Kay Ash

ብዙ ሰዎች በሕይወታችን ካለ ምንም ግብ ነው የሚኖሩት፡፡ ከእነዚህ ካለምንም ግብ ከሚኖሩት ብዙ ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ደግሞ ግብን የማያወጡበት ምክንያት ግብን እንዲያወጡ የሚያደርግ የራእይ አቅጣጫ ስለሌላቸው ነው፡፡ ስለሆነም፣ ብዙ የእውቀት፣ የገንዘብ፣ የልምድ እና የወዳጅ (Connection) ባለጠግነት እያላቸው እንኳን በየቀኑ ፊታቸው የመጣላቸውንና ያገኙትን እያደረጉ፣ አንድም ነገር ሳይገነቡ ጊዜያቸውን ያባክናሉ፡፡

የተሟላና ነገ ስኬትን የሚያስከትል ሕይወትን ለመኖር ከፈለጋችሁ . . .

1. ራእያችሁ ምን እንደሆነ ለይታችሁ እወቁ፡፡ ራእያችሁን ለማወቅ ባላችሁ ጉዞ ትልቁ እንቅፋት የራእይን ትክክለኛ ትርጉም ያለማወቅ መሆኑን አትዘንጉ፡፡

2. ባወቃችሁት ራእያችሁ መሰረት ግቦችን አውጡ፡፡ ግቦቻችሁ የአንድ አመት፣ የአምስት አመትና፣ የአስር አመት የጊዜ ሁኔታዎችን ያካተቱ መሆናቸውን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

3. ባወጣችኋቸው ግቦች መሰረት የየእለት ተግባራዊ እርምጃን ጀምሩ፡፡ ግብ ማለት ነገ የሚደረስበት እቅድ ሲሆን፣ የተግባር እርምጃ ደግሞ ወደ ግቡ የሚወስድ የየእለት እንቅስቃሴ መሆኑን እወቁ፡፡

ራእይ የሌለው ግብ የማውጣት ሙከራ ግራ ያጋባችኋል፡፡ ተግባራዊ እርምጃ የሌለውም ግብ ደግሞ ከምኞት አያልፍም፡፡
ከራእያችሁ አንጻር ግብ አውጡ! ከግቡ አንጻር ደግሞ ስራ ጀምሩ! አንዴ ከጀመራችሁ ደግሞ አታቁሙ!

(ራእይን መገንዘብን አስመልክቶ በቅርቡ የምለቀውን ትምህርት በ YouTube ቻናሌ ይጠብቁ፡፡ እንዲሁም ለሕትመት በመዘጋጀት ላይ ያለውን “ራእይን ማወቅና መኖር” የተሰኘውን አዲስ መጽሐፌን ይጠብቁ፡፡

12/11/2022

ህግ ይኑረን !

ራሱን መቆጣጠር የማይችል ሰው መቼም ቢሆን ነፃ ሊሆን አይችልም ! በህግ የማይመራ ሰው ገደብ የለውም ህግ ማውጣት ወይም ራስን መቆጣጠር ነፃነት የሚነፍግ አሰልቺ የሆነ ነገር ነዉ ተብሎ ይታሰባል ነገር ግን በተቃራኒው ነው ህግ ሲኖረን የምናደርጋቸውን ነገሮች ቅደም ተከተል ስናውቅ ምን ያህል ግዜ እንዳለን እና ነገሮቻችንን መቼ አከናውነን መጨረስ እንደምንችል ጠንቅቀን እናውቃለን ስለዚህ ነፃ ሆንን ማለት አይደለም? ዛሬ አየሩ ከበድ ያለ ነው ፤ ያለውበት ቦታ ምቹ አይደለም እና የመሳሰሉት ሰበቦች ያሰብነውን ከማድረግ ወደ ኋላ እያስቀሩን ከሆነ እኛ ራሳችንን መቆጣጠር አቅቶን ሌሎች ውጫዊ ነገሮች እየመሩን እና እየተቆጣጠሩን ነዉ እና ነፃነታችንን አሳልፈን ለማንም አንስጠው !

መልካም ቀን ምሽት 🙏

የኦቶማን ንጉስ አህመድ ወደ ጦርነት ከመሄዱ በፊት ሚስቱን (ቆንጆዋን ንግሥት) በአንድ ክፍል ውስጥ ቆልፎባት ቁልፉን ለቅርብ ጓደኛው ሙሳ ሰጠው እና "በአራት ቀን ውስጥ ካልተመለስኩ ክፍሉን ...
12/11/2022

የኦቶማን ንጉስ አህመድ ወደ ጦርነት ከመሄዱ በፊት ሚስቱን (ቆንጆዋን ንግሥት) በአንድ ክፍል ውስጥ ቆልፎባት ቁልፉን ለቅርብ ጓደኛው ሙሳ ሰጠው እና "በአራት ቀን ውስጥ ካልተመለስኩ ክፍሉን ክፈት እና ሚስቴን አግባት…”ብሎት ፈረሱ ላይ ወጥቶ ወደ ጦር ሜዳ ሄደ። ከግማሽ ሰዓት በኋላ ንጉሱ ከኋላው አቧራማ ንፋስ እንዳለ አየ። ቆም ብሎ ጓደኛው ወደ እሱ በፍጥነት እየሮጠ ሲመጣ አየ።

"ምነዉ ምን ሆንክ ?" ብሎ ንጉሱ ጠየቀ። በጣም ከመሮጡ የተነሳ ትንፋሹ እየተቆራረጠ ጓደኛው ሙሳ “የተሳሳተ ቁልፍ ነው የሰጠኸኝ” ሲል መለሰ።

ምንድን??? ብሎ አይቶት በድንጋጤ እና በመገረም አየዉ
ቁልፎቹን ከመሞከሩ በፊት ለ4 ቀናት ይቅርና ለ1ሰአት እንኳን አልጠበቀም።

እንደ “ጓደኞችህ” ከምትቆጥራቸው ሰዎች ጋር ተጠንቀቅ እና በትጋት ለምታገኘው ሃብት አደራ ልትሰጣቸው ትችላለህ - እነሱ በቅርቡ እንድትሞት እየተመኙልህ ሊሆን ይችላል እና እራስህን ከጓደኛህም ቢሆን መጠበቅህን አትዘንጋ።

ምክር ብቻ ነዉ።

እሳቤያችሁን ሚዛናዊ አድርጉ!እስከወዲያኛው ድረስ የተረጋጋ ማንነት እንዲኖራችሁ ከፈለጋችሁ፣ በእነዚህ በሁለት ነገሮች ላይ ለመስራት ሞክሩ፡፡1. ራሳችሁ በራሳችሁ ላይ፣ “እንደዚህ ነኝ” ብላች...
12/11/2022

እሳቤያችሁን ሚዛናዊ አድርጉ!

እስከወዲያኛው ድረስ የተረጋጋ ማንነት እንዲኖራችሁ ከፈለጋችሁ፣ በእነዚህ በሁለት ነገሮች ላይ ለመስራት ሞክሩ፡፡

1. ራሳችሁ በራሳችሁ ላይ፣ “እንደዚህ ነኝ” ብላችሁ የምታስትን ሃሳብ ሚዛናዊ አድርጉ፡፡

በራሳችሁ ላይ ያላችሁ ግምት ከመጠን በላይ ከፍተኛ ሲሆን ወይም የዝቅተኝነት ስሜትን የሚያንጻበርቅ ሲሆን ከሰዎች ጋር ያላችሁን ግንኙት ቀስ በቀስ እያጣችሁት ትሄላችሁ፡፡ ሰዎች የሆናችሁትን ሆናችና ቀለል ብላችሁ ስትገኙ ነው የሚፈልጓችሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በራሳችሁ ላይ ያላችሁ እጅግ የወረደው ወይም ከልክ ያለፈ ከፍ ያለው አመለካከት ከተጨባጩ እውነታ ጋር እንድትተላለፉ ያደርጋችኋል፡፡ ነኝ ብላችሁ በምታስቡት ልክ ስትንቀሳቀሱ እውነታው እንደዚያ እንዳልሆነ መገንዘባችሁ አይቀርም፡፡

2. ሰዎች በእናንተ ላይ እንዳላቸው የሚመስላችሁን አመለካከታቸውን ሚዛናዊ አድርጉ፡፡

ሰዎች በእናንተ ላይ ያላቸውን አመለካከት እየገመታቸው ስትኖሩ የስሜት ቀውስ ውስጥ ትገባላችሁ፡፡ በተለይም ሰዎች እንደሚንቋችሁና ችላ እንደሚሏችሁ ማሰብን የመሰለ አደገኛ ሁኔታ የለም፡፡ ሰዎች በእናንተ ላይ ያላቸውን አመለካከት በፈለጉት መልክ የመቅረጽ መብት አላቸው፡፡ ያንንም መቆጣጠር አትችሉም፡፡ የሰዎች አመለካከት ደግሞ በአብዛኛው የሚያንጸባርቀው የእነሱን ንጽረተ-አለም እና አመጣጥ ነው፡፡ እሱን ተወት አድርጉትን በቻላችሁት መጠን ብቁ ማንነትን የመገንባት ስራ ላይ ተጠመዱ፡፡

Dr-Eyob-Mamo

The Valley Of Marvels | Dakhata ValleyThis Dakhata rock has been balancing itself for a long time in the Dakhata Valley,...
10/11/2022

The Valley Of Marvels | Dakhata Valley

This Dakhata rock has been balancing itself for a long time in the Dakhata Valley, eventually becoming a tourist destination.

• The Dakhata Valley is located in Eastern Hararghe.

Yeah, some of the rocks there look like phalluses.

Hunter Gatherers of Ethiopia | The ChabuThe Chabu are one of the world's last remaining hunter gatherer people.• They're...
07/11/2022

Hunter Gatherers of Ethiopia | The Chabu

The Chabu are one of the world's last remaining hunter gatherer people.

• They're situated in Southwest Ethiopia.

• They're rapidly dwindling in size and have been transitioning to more modern living for years now.

ለማን እንደምትሰጡ አስቡበትጊዜያችሁን፣ ገንዘባችሁን፣ ትኩረታችሁን . . . ለማን እንደምትሰጡ በሚገባ አስቡበት፡፡ሰዎቹ ብትሰጧቸው፣ ብትሰጧቸው የማይበቃቸውና በሰጣችኋቸው መጠን እንደገና የሚ...
07/11/2022

ለማን እንደምትሰጡ አስቡበት

ጊዜያችሁን፣ ገንዘባችሁን፣ ትኩረታችሁን . . . ለማን እንደምትሰጡ በሚገባ አስቡበት፡፡

ሰዎቹ ብትሰጧቸው፣ ብትሰጧቸው የማይበቃቸውና በሰጣችኋቸው መጠን እንደገና የሚጠይቁ ከሆኑ ምናልባት እነዚህን እንቁ የሆኑ ሃብቶቻችሁን ትክክለኛ ባልሆነ ሰው ላይ እያፈሰሳችሁ ነው፡፡

ትክክለኛዎቹ ሰዎች . . .

• የምትሰጧቸውን ነገር ያከብራሉ እናንተንም ያመሰግኗችሁማል፡፡

• የምትሰጧቸውን ነገር እንድ እድል እንጂ እንደመብታቸው አይቆጥሩትም፡፡

• መስጠት ባልፈለጋችሁ ወይም ባልቻላችሁ ጊዜ አይነጫነጩም፣ አይከሷችሁም፡፡

• በሰጣችኋቸው ነገር ተጠቅመው ያድረጉበታል እንጂ ባሉበት አይረግጡም፡፡

• በተቻላቸውና አቅማቸው በፈቀደ መጠን ለእናንተም አንድን ነገር ለማድረግ ይሞክራሉ፡፡

Dr-Eyob-Mamo

የብቸኝነት ጉዞ!“እጅግ ከባድ የተባለው ጉዞ ለብቻችሁ የምትጓዙት መንገድ ነው፡፡ ነገር ግን፣ እጅግ በጣም ጠንካራና ብርቱ የሚያደርጋችሁ ጉዞ እሱኛው ጉዞ ነው” (From Lesson Learne...
07/11/2022

የብቸኝነት ጉዞ!

“እጅግ ከባድ የተባለው ጉዞ ለብቻችሁ የምትጓዙት መንገድ ነው፡፡ ነገር ግን፣ እጅግ በጣም ጠንካራና ብርቱ የሚያደርጋችሁ ጉዞ እሱኛው ጉዞ ነው” (From Lesson Learned In Life)

አሁን ያላችሁበትን ጉዞ ብቻሁን እንደተያያዛችሁት ከተሰማችሁ አይዟችሁ፡፡ ይህ ጉዞ ያልቃል፡፡ ይህ ጉዞ ካለቀ በኋላ ግን በምንም ነገር የማይበገር ጥንካሬና ብርታት ይዛችሁ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ፡፡

Dr-Eyob-Mamo

Address

Addis Ababa
212121

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when D.r Eyob Mamo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share