Buna Furniture

Buna Furniture የአርሰናል እግርኳስ ክለብን የሚመለከቱ መረጃዎች የሚቀርቡበት ቻነል
Arsenal Football club Info channel

የአርሰናል ሌጀንድ" ሄነሪ ...! ልዩ ዳሰሳ    #አርሰናል  #ሄነሪ
17/08/2026

የአርሰናል ሌጀንድ" ሄነሪ ...! ልዩ ዳሰሳ #አርሰናል #ሄነሪ

"የንጉሱ ልደት የአርሰናል ሌጀንድ Thierry Henry! " ቅጽበቶች ትንተና 🏆 #አርሰናል #የፕሪሚየርሊ...

የማድሪድ ፍላጎት ለዙቢሜንዲ ሪያል ማድሪድ ማርቲን ዙቢሜንዲን ለማዘዋወር በድጋሚ ፍላጎት ማሳየቱ ተዘገበ።አዲሱ የማድሪድ አሰልጣኝ ሆሴ ሞሪንሆ የአርሰናሉን አማካይ ዝውውር በመደገፍ ተጫዋቹን ...
17/08/2026

የማድሪድ ፍላጎት ለዙቢሜንዲ

ሪያል ማድሪድ ማርቲን ዙቢሜንዲን ለማዘዋወር በድጋሚ ፍላጎት ማሳየቱ ተዘገበ።

አዲሱ የማድሪድ አሰልጣኝ ሆሴ ሞሪንሆ የአርሰናሉን አማካይ ዝውውር በመደገፍ ተጫዋቹን ለማስፈረም የሚያደርገውን ጥረት ማጽደቃቸውን ቲምቶክ ነው የዘገበው። 🇪🇸

ዙቢሜንዲ ማድሪድን የመቀላቀል እድል ቢገኝ ደስተኛ ሲሆን፣ አርሰናሎች ደግሞ ተገቢው የዝውውር ሂሳብ ከተቀረበላቸው ተጫዋቹን ለመሸጥ ፈቃደኛ ናቸው ተብሏል።

መድፈኞቹ ባለፈው ክረምት ለተጫዋቹ ዝውውር 65 ሚሊዮን ዩሮ መክፈላቸው ቢታወቅም አሁን ለዝውውሩ የሚጠይቁት ዋጋ ግን እስካሁን አልተወሰነም።

(ምንጭ፦ )

​ #ሪያልማድሪድ #አርሰናል #አርሰናል❤❤❤ 💞😘👑🙌

13/07/2026

የፔሩ ህጻናት ስያሜ ሆኗል ሃላንድ 👶🇵🇪

በፔሩ ከተወለዱ ህጻናት አብዛኛዎቹ ሃላንድ የሚል ስያሜ እንዲወጣላቸው ተሰማ።
𝐇𝐚𝐚𝐥𝐚𝐧𝐝 𝐢𝐬 𝐞𝐯𝐞𝐫𝐲𝐰𝐡𝐞𝐫𝐞. 🔥
#𝐇𝐚𝐚𝐥𝐚𝐧𝐝 #ሃላንድ #ፔሩ #እግርኳስ #አለምዋንጫ

አርጀንቲና ስዊዘርላንድን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ተሸጋገረችበ23ኛው የዓለም ዋንጫ አርጀንቲና  ስዊዘርላንድን 3ለ1 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ተሸጋግራለች።በካንሳስ ሲቲ ስታዲየም በተደረገ...
12/07/2026

አርጀንቲና ስዊዘርላንድን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ተሸጋገረች

በ23ኛው የዓለም ዋንጫ አርጀንቲና ስዊዘርላንድን 3ለ1 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ተሸጋግራለች።

በካንሳስ ሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አሌክሲስ ማካሊስተር ለአርጀንቲናን ፣ ዳን ንዶይ ደግሞ ለስዊዘርላንድ ግብ አስቆጥረው መደበኛው 90 ደቂቃ 1ለ1 ተጠናቋል።

ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ ሲያመራ ሁሊያን አልቫሬዝ እና ላውታሮ ማርቲኔዝ አስቆጥረው ጨዋታው በአርጀንቲና 3ለ1 አሸናፊነት ተደምድሟል።

በጨዋታው አጥቂው ብሪል ኢምቦሎ 72ኛው ደቂቃ ላይ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱ ስዊዘርላንድን ዋጋ አስከፍሏል።

የ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ አርጀንቲና በግማሽ ፍፃሜው ከእንግሊዝ ጋር ትጫወታለች።

#አርጀንቲና #ሜሲ

አርሰናል ግብ ጠባቂ አስፈረመአርሰናል ከሊድስ ዩናይትድ በቅርቡ የለቀቀውን ግብ ጠባቂ፣ ኢላን መሊሬን በነፃ ዝውውር አስፈረመ። ​በሊድስ ዩናይትድ ቤት ሰባት የውድድር ዘመናትን ያሳለፈው መሊሬ...
09/07/2026

አርሰናል ግብ ጠባቂ አስፈረመ
አርሰናል ከሊድስ ዩናይትድ በቅርቡ የለቀቀውን ግብ ጠባቂ፣ ኢላን መሊሬን በነፃ ዝውውር አስፈረመ።

​በሊድስ ዩናይትድ ቤት ሰባት የውድድር ዘመናትን ያሳለፈው መሊሬ፣ 215 ጨዋታዎችን በማድረግ ክለቡ ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ትልቅ እገዛ አድርጓል።

ባለፈው የውድድር ዘመን ማጠናቀቂያ ላይ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ክለቡን መልቀቁ ይታወሳል።

​የእርሱ ወደ መድፈኞቹ ቤት መምጣት ከዳቪድ ራያ እና ኬፓ አሪዛባላጋ ጎን ለጎን የአርሰናልን የግብ ጠባቂ አማራጮች ይጨምራል።

በተጨማሪም ይህ ዝውውር ከወጣቱ እንግሊዛዊ ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ተጨማሪ የመጫወት ዕድል እንዲያገኝ፣ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን በውሰት ውል ለቆ እንዲወጣ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል።

#አርሰናል #ዝውውር

የጉማሬሽ አርሰናል ዝውውር      #አርሰናል  💞😘👑🙌
08/07/2026

የጉማሬሽ አርሰናል ዝውውር
#አርሰናል 💞😘👑🙌

01/07/2026

የትሮሳርድ ዝውውር
#አርሰናል #አርሰናል

26/06/2026

ጉማሬሽ ወደ አርሰናል #አርሰናል #ዝውውር

አርሰናል ፒዬሮ ሂንካፒዬን በቋሚነት አስፈረመአርሰናል ፒዬሮ ሂንካፒዬን ከባየር ሌቨርኩሰን በውሰት ካመጣበት ውል ላይ የነበረውን ቋሚ የማድረግ አማራጭ (option) ተግባራዊ አድርጓል።​ተከላ...
25/06/2026

አርሰናል ፒዬሮ ሂንካፒዬን በቋሚነት አስፈረመ

አርሰናል ፒዬሮ ሂንካፒዬን ከባየር ሌቨርኩሰን በውሰት ካመጣበት ውል ላይ የነበረውን ቋሚ የማድረግ አማራጭ (option) ተግባራዊ አድርጓል።

​ተከላካዩ ባለፈው ክረምት ከሌቨርኩሰን በውሰት አርሰናልን የተቀላቀለ ሲሆን፣ ክለቡ ከ22 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን እንዲያነሳ አግዟል።

​ስካይ ስፖርትስ ኒውስ እንደተረዳው ከሆነ፣ ለሂንካፒዬ የተከፈለው የዝውውር ዋጋ 34.5 ሚሊዮን ፓውንድ ገደማ የ24 ዓመቱ ተከላካይ የ5 ዓመት ኮንትራት ፈርሟል።

​ሂንካፒዬ ባለፈው የውድድር ዓመት በሁሉም ውድድሮች 39 ጨዋታዎችን ለአርሰናል ያደረገ ሲሆን፣ አርሰናል እና ፓሪስ ሴንት ዠርሜንን (PSG) በተጋጠሙበት የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ላይም በቋሚነት ተሰልፎ ተጫውቷል።
​ #አርሰናል #የዝውውርዜና #ፒዬሮሂንካፒዬ #የእንግሊዝፕሪሚየርሊግ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Buna Furniture posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share