Menen Daniel

Menen Daniel Model and actors

✍️✍️ሰላም የተወደዳቹ፦የዛሬ ውሎዬን እስኪ ላካፍላቹ። 👉 ዛሬ ማለዳዬ ቆንጆ ነበር ፤ እናም ንቅት ንቅትቅት ብዬ ወደ ስራዬ አዘገምኩ። በነገራችን ላይ ማለዳ ያበጃጀነው ፣ የሰነቅነው ሀሳብ፣...
13/07/2026

✍️✍️ሰላም የተወደዳቹ፦
የዛሬ ውሎዬን እስኪ ላካፍላቹ።
👉 ዛሬ ማለዳዬ ቆንጆ ነበር ፤ እናም ንቅት ንቅትቅት ብዬ ወደ ስራዬ አዘገምኩ። በነገራችን ላይ ማለዳ ያበጃጀነው ፣ የሰነቅነው ሀሳብ፣ ፀሎት፣ አመጋገብ፣ በማለዳ የሰማናቸው ቃላቶች እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ያማረ የሰመረ ወይም የተዛባ ቀን እንድንውል እንገደዳለን። እናም ማለዳቹ ላይ መጠንቀቅ መልካም ነው። እኔ በበኩሌ በማለዳ የማውራት ልምድ የለኝም እስከ ረፋድ በዝምታ ነው የምቆየው በቻልኩት መጠን ማታ ስተኛ የማስበውን ሀሳብ አስተካክላለሁ ምክንያቱም ማለዳ ላይ አዕምሮዋችን ካቆመበት ነው የሚቀጥለው ስለዚህ ማታ ሀሳባችንን መልካም ሀሳብ ላይ ካስቆምነው የጠዋት ሀሳብ ሰላማዊ ነው። በተቻለ መጠን ሰው ሲተኛ እና ሲነሳ መፀለይ አለበት ባይ ነኝ።እና በራሴ ወሬ ያዝኳቹ ፦
👉እናም ወደ ቢሮዬ ገባሁ ጓደኞቼን ሰላም ብዬ ወደ ስራዬ ገባሁ። በመሀል አንዱ የስራ ባልደረባችን አልገባም እና ለምን እንዳልገባ ጠየቅኳቸው። ከመሀል አንዷ ''አሞታል'' አለችኝ። ደንግጬ፦ እእእእእ መቼ ? ቅዳሜ አሉኝ ። ውይ ሲያሳዝን አልኩ እና ስልክ ልደውል ሳወጣ። ''ሄደሽ አትጠይቂውም''
አይ ዛሬ እንኳን ከእህቴ ጋር ሌላ የታመመ ሰው እጠይቃለሁ እሷ ትጠብቀኛለች ከስራ ስወጣ፤ ''እናንተ ጠየቃቹት?''
አዎ ሁለታችን ትላንት ጠይቀነዋል። አንዷ ግን አልጠየቀችውም ነበር። እና እኔ እኮ ከአንቺ ጋር እጠይቀዋለሁ ብዬ ነበር አለችኝ። እንዴት ይሻላል ታዲያ ብዬ እያሰብኩ እያለ ፣ ሌሎቹ መሳቅ ጀመሩ አልገባኝ ነበር እና። ምነው? አልኳቸው'' አይ እሷ ብቻዋን ልትሄድ ስለሆነ ነው። ከዛ አሰብ አድርጌ ፤ ሀሳብ እንድትሰጠኝ ጠየቅኳት፦ እእእእእ በቃ እጠይቀዋለሁ ብቻዬን አለች። እሺሺሺ አልኳት ግን ፊቷ ላይ ፦ቅሬታ ፣ፍርሀት ፣አለመመቸት ይታያል። የነሱ ሳቅ የእሷ ሁኔታ ጥያቄ ስለፈጠረብኝ እእእእእ ለምን እንደዚህ አላቹ አስረዱኝ እስኪ አልኳቸው። በመሀል አንዷ ቸኮል ብላ፦ እሷ እኮ ወንድ ቤት መሄድ አትወድም አለችኝ። እኔም ቀበል አድርጌ በእርግጥ ብቻዋን ባትሄድ ይመረጣል ታሞም ቢሆን ተሰብስቦ ይሻላል የስራም ባልደረባም ቢሆን አልኳት። ቀበል አለችና ደሞ ይወዳታል አለችኝ፦ በእርግጥ ሀሳቡ ለእኔ አዲስ ቢሆንም ለማሳለፍነ ሞከርኩ። የጉዳዩ ባለቤት ማውራት ጀመረች። ፨
👉ይሄውልሽ እኔ ህይወቴን ታውቂዋለሽ ከብዙ ነገር መራቅ አለብኝ፤ ሲጀምር እኔ በታሪክ ወንድ ቤት እንደመሄድ የምጠላው ነገር የለም ትክክል ነው ብዬም አላምንም። አሁን ደሞ አስቢው እኔ የስራ ባልደረባዬ ነው በጠይቀው እናንተ እውነቱን ታውቃላቹ ፣ ያየኝ ሰው ደሞ የሚገምተው ሌላ ነው። እራሴን ለግምት ማስቀመጥ አልፈልግም ። እንዲገምቱሽ እድል ከሰጠሽ በኋላ ለግምታቸው ምላሽ መስጠት፣ እውነቱን ለማስረዳት መጣር ለእኔ ሌላ ስራ ነው የሚሆንብኝ ስለዚህ ከዛ ነገር እሩቅ ለመሆን ነው ሁሌም ፍላጎቴ አለች ። እርግጥ እኔም እደግፋታለሁ ሴት ወንድ ቤት መሄድ የለባትም።ደሞም ተረድቻታለሁ የቤተክርስቲያን ልጅ ናት የራሷ መመሪያ አላት፣ ሰዎች በሷ እንዲሰናከሉ አትፈልግም፣ እሷ የቤተክርስቲያን ልጅ ሆና እንዲህ ካደረገች ብሎ ሰው በእሷ እንዲስት አትፈልግም ። እኔ ግን የምለው ሰዎች የሚያዩት ላይ ፈራጆች፣ ገማቾች ናቸው። ሰው በስንት የክፋት መንገድ እየተጓዘ የራሰን ጉድለት ሀጢያት ከማየት ጣቶቹን በሌሎች ስራ ህይወት ላይ ሲጠቁም ይኖራል። የሰው ልጅ አትፍረድ እየተባለ ይፈርዳል፣ ይከሳል፣ የሱን ዶሴ ቢገለጥ ተነቦ አያልቅም። እናም ልል የፈለኩት የሰው ልጅ የሌሎችን ህይወት በመገመት እና እራሱን በፃድቅ ቦታ አስቀምጦ ከሚመፃደቅ የራሱን ኑሮ ለምን አይኖርም። ፈራጅ፣ አፅዳቂ ወዳጅ እግዚአብሔር አለ።ሰውን ሲበድል እንጂ ንስሀ ሲገባ አላየህም እና አትፍረድ። ይላሉ አበው።መልካም አመሻሽ ይሁንላቹ። ስለ ሰው ከማውራታቹ በፊት እራሳቹን መርምሩ።✝️🙏💒የክርስቶስ ምህረት፣ ፍቅር፣ ርህራሄ፣ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን።

በነገራችን ላይ ዛሬ የተደራረበ ድርብ ሰንበት ነው እንኳን አደረሳቹ አደረሰን። 👉  ዛሬ የፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ መታሰቢያቸው ነው።👉 የእግዚያብሔር መልካም እቃው ...
12/07/2026

በነገራችን ላይ ዛሬ የተደራረበ ድርብ ሰንበት ነው እንኳን አደረሳቹ አደረሰን።
👉 ዛሬ የፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ መታሰቢያቸው ነው።
👉 የእግዚያብሔር መልካም እቃው የጳውሎስ እና የችኩሉ የቅን ልብ የእግዚአብሔር ወዳጅ የጴጥሮስ መታሰቢያ ባዐላቸው ነው
👉 እንዲሁም ሰንበተ እሁድን ጨምሮ ድርብርብ በዓል
ነው።
👉ሌላው የሀዋሪያት ፆም የሚፈታበት ቀን ነው።
እንኳን አደረሰን በዓሉን በፅድቅ እንድናሳልፈው የቀና ልቦና የሚራራ፣ ለተቸገረ የሚዘረጋ እጆችን ያድለን። ከቻልን አካፍለን ካልቻልን ራርተን ቢኖረን እንደምናደርግ አስበን በበጎ በፅድቅ የምንውልበት እለተ ሰንበት ያድርግልን።እግዚአብሔር የክፋታችንን መንገድ ሳይመለከት በትዕግሥት የጠበቀን ምህረቱን ከእኛ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን። የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን። የፃድቃን ፀጋ በረከታቸው ከሁላችንም ጋር ይሁን። አሜን 🙏💒✝️

✍️✍️✍️ አንድ ሰው ምን ሲል ሰማሁት፦እኔ ትልቁ ስኬቴ ሚስቴን ያገባሁ ቀን ነው የጀመረው አለ። ቀጠለ ፦እኛ ልጆች ወለድን ግን ደስታዬ ሚስቴ ናት ከዛ ቀጥሎ ነው በልጆቼ የምደሰተው።👉 ሚስ...
11/07/2026

✍️✍️✍️ አንድ ሰው ምን ሲል ሰማሁት፦
እኔ ትልቁ ስኬቴ ሚስቴን ያገባሁ ቀን ነው የጀመረው አለ። ቀጠለ ፦
እኛ ልጆች ወለድን ግን ደስታዬ ሚስቴ ናት ከዛ ቀጥሎ ነው በልጆቼ የምደሰተው።
👉 ሚስቴ በየቀኑ ሙሽራዬ ናት
👉ሚስቴ ሁልጊዜ ፍቅረኛዬ ናት
👉ከሚስቴ ጋር ሁልጊዜ በአዲስ ፍቅር ይዘኛል
👉 ሁሌም እንደመጀመሪያው ገዜ አይኖቿን እያየሁ እንደማፈቅራት እነግራታለሁ።
👉 ከልጆቼ ቀድሜ ያገኘኋት ሚስቴን ነው እስከ ሞቴም የምኖረው ከሚስቴ ጋር ነው።
👉 ብዙ ሰው ሰላምን ፣ ደስታን በልጆች ውስጥ ይፈልጋል። ግን ደስታ ያለው ከሚስት ውስጥ ነው። እናት እና አባት ደስተኞች ሲሆኑ ልጆች ደስተኞች ይሆናሉ። እኔ ሁልጊዜ እሰራለሁ የምሰራው ለደስታዬ ነው ስለዚህ በምጓዘው ጉዞ ሁሉ ደስተኛ ነኝ። ደስታዬ ሚስቴ ናት ለእሷ እሰራለሁ ለቤተሰቤ እሰራለሁ። የምኖረው ለነሱ ነው እሱ ያስደስተኛል። እንዲህ ሲል ሰማሁት ተደንቂያለሁ ።💪። ሰው የሚኖርለት አላማ ሲኖረው አላማውንም በአግባቡ ሲያውቀው ደስ ይላል።

እናንተ፣ በልጅነታቹ ምን መሆን ነው የምትፈልጉት ስትባሉ መልሳችን የሁላችንም የተለያየ ነበር አይደል? አድገንም የልጅነት ህልማችንና አሁን ያለን ህይወት የተለያየ ነው። የእኔ የልጅነት ህልም...
04/07/2026

እናንተ፣ በልጅነታቹ ምን መሆን ነው የምትፈልጉት ስትባሉ መልሳችን የሁላችንም የተለያየ ነበር አይደል? አድገንም የልጅነት ህልማችንና አሁን ያለን ህይወት የተለያየ ነው። የእኔ የልጅነት ህልም ምን እንደነበር ልንገራቹ፦ እኔ ዶክተር መሆን ነበር ምኞቴ ከዶክተርም የጤና መኮንን መሆን ነበር እስከ 11ኛ ክፍል ህልሜ ከዛ ተለወጠ እና ሞዴል ሆንኩ በዛው አያይዤ በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ያዝኩ ። አሁን ብር መቁጠር እና ሰዎችን መመርመር ምን አንድ አደረገው🤔 አይ ጉድ እኮ ነው። ሌላውስ ልጅ ሆኜ ምን እንደምል ታውቃላቹ አባቴ ገበሬ ነው እና ማረሻ ትራክተር እገዛልሀለው አልኩት😁 ከዛስ እኔ በጣም ሀብታም እሆናለሁ ከራሴ አልፌ ለብዙ ሰዎች ስራ ፈጣሪ እሆናለሁ ከልኩ።😁😉 ሀሀሀሀ እረ አሁን እንኳን ስራ ፈጣሪ ልሆን እኔም ስራ አጥ ወጣት ሆኛለሁ 😁😉 አሁን ማነው ተጠያቂ ሆሆሆ ። ቀልዱ ይብቃ እና በልጅነታችን እንደምንመኘው ህይወት አልጋ በአልጋ ቢሆን ምድር ገነት ትሆን ነበር። ባለ ሀብት ሆኖ ሀገር ለሀገር መዞር ትልልቅ ድርጅቶችን መክፈት 😉😁 ብቻ ምኞቴ ብዙ ነበር። አሁን ግን ትልቁ ምኞቴ እግዚአብሔር ብቻ ነው። እኔ በአቅሜ ሮጬ አልሆነም ከሁን እግዚአብሔር የፈቀደው ይሁን። ታውቃላቹ እግዚአብሔር አሰራሩ በጣም ረቂቅ ነው። ለአንዳንዱ ይሰጠዋል ለአንዳንዱ ይከለክለዋል። ምን ብትለፋ እግዚአብሔር ካልፈቀደ አይሆንም። ልጆቹን እንዴት እንደሚጠብቅ ያውቃል። ቢሰጠን የምንጠፋ ልጆቹን ከልክሎ በቤቱ እያስተማረ ያቆየናል። ባይሰጣቸው የሚጠፉትን ሰጥቷቸው ይጠብቃቸዋል። ቢሰጣቸውም ቢከለክላቸውም አስቸጋሪዎቹን ሰጥቷቸው ሁሉንም አይተው ሲበቃቸው እንዲመለሱ ይለቃቸዋል። እግዚአብሔር ረቂቅ አሰራር አለው። ፀሎት የዘገየባቹ የመማሪያ ጊዜ መሆኑን አትርሱ ባይሰጣችሁም አመስግኑ የተሰጣቹ ዛሬ ነው። የእለት እንጀራን ያልከለከለ አምላክ የልባቹን መሻት አሳዩት አይከለክላቹም አምናቹ ጠብቁት በምስጋና። በሁሉ ትክክል ነው እና ተመስገን። 🙏💒💓✝️

14/06/2026

11/06/2026

New arrivals from usa 🇺🇸✅ Clerk (first quality)👌አልቆ ድጋሚ የገባ /Re-enterMade in  USE  🇺🇸Size #40 #41  #42  #43  #44🔴FREE DE...
01/05/2026

New arrivals from usa 🇺🇸
✅ Clerk (first quality)👌
አልቆ ድጋሚ የገባ /Re-enter
Made in USE 🇺🇸
Size #40 #41 #42 #43 #44
🔴FREE DELIVERY(ያሉበት ቦታ ያለተጨማሪ ክፍያ እናደርሳለን🏍)
📶0901917096
🔻🔻🔻https://t.me/etegea
🏠address Gerji

New arrivals from usa 🇺🇸✅ECCO (first quality)👌አልቆ ድጋሚ የገባ /Re-enterMade in  USE  🇺🇸Size #40 #41  #42  #43  #44🔴FREE DELI...
29/04/2026

New arrivals from usa 🇺🇸
✅ECCO (first quality)👌
አልቆ ድጋሚ የገባ /Re-enter
Made in USE 🇺🇸
Size #40 #41 #42 #43 #44
🔴FREE DELIVERY(ያሉበት ቦታ ያለተጨማሪ ክፍያ እናደርሳለን🏍)
📶0901917096
🔻🔻https://t.me/etegea
🏠address:Gerji

Address

28-78031
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Menen Daniel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share