World Class Quality Award Organization

World Class Quality Award Organization award for an outstanding achievements that has saved the world and its peoples

«ጥራት የቀደምትነታችን መለያና ለዓለም ምሳሌ የሚያደርገን የብሔራዊ ክብራችን ማህተም ነው! »
01/09/2026

«ጥራት የቀደምትነታችን መለያና ለዓለም ምሳሌ የሚያደርገን የብሔራዊ ክብራችን ማህተም ነው! »

"ጥራት የብሔራዊ ክብራችን ማህተም ነው!"
31/08/2026

"ጥራት የብሔራዊ ክብራችን ማህተም ነው!"

 #ወርልድ ክላስ የጥራት ሽልማት ድርጅት የጥራት ሽልማት ተሸላሚ ተቋማትን ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ይሸልማል!
26/08/2026

#ወርልድ ክላስ የጥራት ሽልማት ድርጅት የጥራት ሽልማት ተሸላሚ ተቋማትን ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ይሸልማል!

 #ማሳሰቢያ:-ከድርጅታችን ጋር ተቀራራቢ ስም አውጥተው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ ተቋማት መኖራቸውን እና ደንበኞቻችን መደናገራቸውን እያሳወቁን ይገኛሉ።  #የእኛ ትክክለኛ መጠሪያ ከላይ ያለው ነ...
26/08/2026

#ማሳሰቢያ:-ከድርጅታችን ጋር ተቀራራቢ ስም አውጥተው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ ተቋማት መኖራቸውን እና ደንበኞቻችን መደናገራቸውን እያሳወቁን ይገኛሉ።
#የእኛ ትክክለኛ መጠሪያ ከላይ ያለው ነው።
#ደንበኞቻችን የእኛ ድርጅት መጠሪያዎች በኢትዮጵያ የንግድ ህግ መሰረት የተመዘገበና ላለፉት 32 ዓመታት በነባር አገልግሎቶቻችን የምንታወቅ መሆኑ አይዘነጋም።
#ለየትኛውም መረጃ በየገፆቹ ላይ ባሉት ስልኮች ያረጋግጡ!

📌ለክልል ስራ አመልካቾች ዛሬ ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና ቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን ከ3:00  ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል። 📌በመሆኑም በሰዓቱ ጠብቃ ፈተናችሁን በመመሪያው መሠረት ውሰዱ።📌አዲስ አመል...
26/08/2026

📌ለክልል ስራ አመልካቾች ዛሬ ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና ቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል።

📌በመሆኑም በሰዓቱ ጠብቃ ፈተናችሁን በመመሪያው መሠረት ውሰዱ።

📌አዲስ አመልካቾች በማስታወቂያው ላይ የተገለፀውን መሰረት አድርጋችሁ አመልክቱ።

📌በማስታወቂያው ላይ የተቀመጡ መስፈርችን የማያሟሉ አመልካቾች ማመልከቻ ተቀባይነት አይኖረውምደ
♻️♻️♻️♻️

 #የጥራት ስርዓት ዝርዓታ መረጃ መስጠትን ይመለከታል፡፡ #ወርልድ ክላስ የጥራት ሽልማት ድርጅት ህጋዊ ፈቃድ ኖሮት ተቋማትን በአፈጻጸም ልህቀትና በጥራት ሽልማት መለኪያ መስፈርት መዝኖ ለመሸ...
20/08/2026

#የጥራት ስርዓት ዝርዓታ መረጃ መስጠትን ይመለከታል፡፡
#ወርልድ ክላስ የጥራት ሽልማት ድርጅት ህጋዊ ፈቃድ ኖሮት ተቋማትን በአፈጻጸም ልህቀትና በጥራት ሽልማት መለኪያ መስፈርት መዝኖ ለመሸለም የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡ ድርጅታችን የሀገራችን ዜጎችና ተቋማት በጥራት ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ከነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም የሚቆይ የጥራት ንቅናቄ አዘጋጅቷል፡፡ በንቅናቄው ቆይታ ሊሰራቸው ካሰባቸው ስራዎች መሀከል አምራችም ሆኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስለ ጥራት ስራ አመራር ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው፡፡
አንድ ድርጅት ውስጥ ውጤታማ የጥራት አስተዳደር ሥርዓት (Quality Management System) ለመዘርጋትና ሥራ ላይ ለማዋል ከታች የተዘረዘሩት አምስት መሠረታዊ የጥራት አንኳር ስራዎች መኖራቸው ተቋሙ በገበያ ውስጥ መልካም ስም ያለውና አስተማማኝ እና ህጋዊ ተቋም ለመገንባት አስፈላጊ ናቸው፡፡
1. የጥራት ፖሊሲ ( QUALITY POLICY )፡- የድርጅቱ የበላይ አመራር ስለ ጥራት ያለውን አጠቃላይ አቅጣጫ፣ ቁርጠኝነትና ዓላማ የሚገልጽበት ይፋዊ ሰነድ ነው። ይህ ፖሊሲ በድርጅት ውስጥ የሚተገበርበት መንገድ የድርጅቱን ራዕይና ተልዕኮ መሠረት ያደረገ አጭርና ግልጽ የጥራት መግለጫ በማዘጋጀት ፣ ፖሊሲው ለሁሉም ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላት እንዲደርስና እንዲገባቸው ማድረግ እና ፖሊሲው ከISO 9001 ወይም ከሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ሁለተኛው የባለሙያው የሥራ ዝርዝር (Job description and Responsibilities ) ሲሆን ይህም ከበላይ አመራሩ ጋር በመሆን የድርጅቱን የጥራት ፖሊሲ ማዘጋጀት ፣ መከለስና ማዘመን እና የጥራት ፖሊሲው በሁሉም የድርጅቱ ክፍሎች በውጤታማነት መተዋወቁንና መተግበሩን መከታተል ነው፡፡ ፖሊሲው ግልጽና የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ተገቢ የህግ ማዕቀፍ ሆኖ ያገለግላል፡፡
2. የጥራት ዕቅድ (QUALITY PLANNING)፦ የጥራት ዓላማዎችን የመለየት፣ ዓላማዎቹን ለማሳካት የሚያስፈልጉ የሥራ ሂደቶችን (Processes)፣ ግብዓቶችንና መስፈርቶችን የማዘጋጀት ሂደት ነው፡፡ በድርጅት ውስጥ የሚተገበርበት መንገድ በተመለከተ ሊለኩ የሚችሉ የጥራት ግቦችን (SMART Quality Objectives) በየክፍሉ ማስቀመጥ ፣ የምርት ወይም አገልግሎት ደረጃና የስራ መመሪያዎችን (Standard Operating Procedures-SOPs) ማዘጋጀት እና ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን (የሰው ኃይል፣ መሣሪያዎች ፣ ወዘተ) መመደብ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም የተመደበውን የጥራት ባለሙያ እና የባለሙያው የሥራ ዝርዝር (Job description and Responsibilities) በጥሩ ሁኔታ ዘርዝሮ መስጠት ለስራው ውጤታማነት የግድ ነው፡፡ ሌላው የድርጅቱን ዓመታዊና የረጅም ጊዜ የጥራት ዕቅድ ( Quality Management Plan ) ማዘጋጀት የግድ ነው፡፡ ለእያንዳንዱ ምርት/አገልግሎት ደረጃቸውን የጠበቁ የአሠራር መመሪያዎችን (SOPs) እና የማረጋገጫ ዝርዝሮች (Checklist) ማዘጋጀት ይገባል፡፡ የጥራት ግቦች (KPIS) መሳካታቸውን የሚለኩ መለኪያዎችን መቅረጽም ያስፈልጋል፡፡
3. የጥራት ቁጥጥር (QUALITY CONTROL - QC)፦ የሚመረተው ምርት ወይም የሚሰጠው አገልግሎት የተቀመጠውን ስታንዳርድ ማሟላቱን ለማረጋገጥ የሚደረግ የፍተሻና የመለካት (Inspection & Testing) ሥራ ነው። ዋና ትኩረቱ በምርቱ/በአገልግሎቱ ጥራት ላይ ነው:: በድርጅት ውስጥ የሚተገበርበት መንገድም የገቡ ግብዓቶችን ( Raw materials )፣ በሂደት ላይ ያሉና ያለቁ ምርቶችን በመመርመርና በመፈተሽ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት የተበላሹ ወይም ስታንዳርዱን ያላሟሉ ምርቶችን ለይቶ ማስወገድ ወይም ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡ የፍተሻ ውጤቶችን በስታቲስቲክስ መዝግቦ መያዝ ( Statistical Process Control ) በመያዝ ለማረሚያ መጠቀምም ይገባል፡፡ ሌላው የጥራት ቁጥጥር ቁልፍ ነገር የባለሙያው የሥራ ዝርዝር (Job description and Responsibilities) ነው፡፡ ከስራ መዘርዝሩ በመነሳትም ሰራተኛው ዕለታዊ የጥራት ፍተሻዎችንና የመስክ/የላብራቶሪ ምርመራዎችን ማካሄድ ወይም መከታተል ይኖርበታል፡፡ ጉድለት ያለባቸውን ምርቶች/አገልግሎቶች በመለየት የማስተካከያ እርምጃ (Corrective Action) እንዲወሰድ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ የጥራት ቁጥጥር ሪፖርቶችን በየቀኑ/በየሳምንቱ ማዘጋጀትና ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4. የጥራት ማረጋገጫ (QUALITY ASSURANCE - QA) ፦ ይህ ተግባር ምርቱ ወይም አገልግሎቱ የሚፈልገውን ጥራት አሟልቶ እንዲወጣ የሥራ ሂደቱን (Process) የማሻሻል ፣ የቅድመ-መከላከያ ሥርዓት የመዘርጋትና የመከታተል ሂደት ነው፡፡ ዋና ትኩረቱ ሂደቱ ላይ ነው፡፡
ይህም በድርጅቱ ውስጥ የሚተገበርበት መንገድ በቅድሚያ የውስጥ የጥራት ኦዲት (Internal Quality Audit) በየጊዜው ማካሄድ ፣ ሠራተኞች በተዘጋጁ የስራ መመሪያዎች (SOPs) መሠረት እየሠሩ መሆናቸውን መከታተል ፣ ማረጋገጥ ፣ የጥራት ስጋቶችን (Risks) አስቀድሞ በመለየት የመከላከያ እርምጃዎችን መውሰድ የሚሉት ናቸው፡፡ ቀጣዩ ክፍል ከላይ እንደተገለጽነው የባለሙያው የሥራ ዝርዝር (Job description and Responsibilities) መስጠት ሲሆን የድርጅቱን የውስጥ ኦዲት (Internal Auditing) መርሐ-ግብር ማዘጋጀትና ኦዲት ማካሄድ ፣ የአሠራር ሂደቶች ከISO እና ከሀገሪቱ ሕጎችና ደረጃዎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ እና ለሠራተኞች የጥራት ግንዛቤና የአሠራር ሥልጠናዎችን መስጠት የስራው ዋና ዋና ክፍሎች ናቸው፡፡
5. የጥራት ማሻሻያ (Quality Improvement – QI )፦ የድርጅቱን የሥራ ሂደቶችና የውጤት ጥራት በተስተካከለ ሁኔታ ለማሳደግና ብክነትን ለመቀነስ የሚደረግ ተከታታይ ጥረት ነው ( Continuous Improvement/Kaizen )፡፡ ይህም በድርጅቱ ውስጥ የሚተገበርበት መንገድ በቅድሚያ የደንበኞችን አስተያየት (Customer Feedback) እና ቅሬታዎች መተንተን ፣ መሰብሰብ ፣ ማደራጀት ፣ መለየት ፣ የችግሮችን ሥረ-መንስኤ በመለየት ድጋሚ እንዳይከሰቱ ማድረግ እና እንደ Kaizen, Lean, ወይም Six Sigma ያሉ የጥራት ማሻሻያ ፍልስፍናዎችን መተግበር ግድ ነው፡፡ የደንበኞች አስተያየትና ቅሬታዎችን በመተንተን የማሻሻያ ፕሮጀክቶችን መቅረጽ ፣ የችግሮች ሥረ-መንስኤን ለመለየት የሚያስችሉ መሣሪያዎችን በመጠቀም መፍትሔ ማመንጨት ፣ የጥራት ማሻሻያ ቡድኖችን ማደራጀትና መምራት ይገባል፡፡
#ተቋማት ጥራት የሌለው ምርትና አገልግሎት ሰጥተው ለአደጋ ከሚዳረጉ ከላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ውጤታማ ተቋም እንዲኖራቸው ማድረግ እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡ ገንዘብ ያወጡ ይሆናል ፣ ይደክሙ ይሆናል ፣ ምንም ቢሆኑ የድርጅቱ ህልውና ወሳኝ በመሆኑ የጥራት አስተዳደር ሥራ ባለሙያ (Quality Management Manager/Officer) በመቅጠር/በመመደብ በድርጅቱ ውስጥ የተቀናጀ የጥራት አስተዳደር ሥርዓት በመዘርጋት የምርት/አገልግሎት ጥራትን ማረጋገጥና ተከታታይ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ሙያተኛ ዋና ስራው ከላይ የተዘረዘረውን በሙሉ በተግባር ማዋል ፣ የጥራት ፖሊሲና ዕቅዶችን ማዘጋጀትና መከታተል ፣ የውስጥ ኦዲት ማካሄድና የጥራት ማረጋገጫ (QA) ሥርዓቱን መምራት ፣ የጥራት ቁጥጥር (QC) ፍተሻዎችን መቆጣጠርና ሪፖርት ማቅረብ ፣ የደንበኞች ቅሬታ መነሻዎችን በመተንተን የጥራት ማሻሻያ (QI) ፕሮጀክቶችን መምራት እና ለሠራተኞች የጥራት ደረጃዎና አሠራሮች ሥልጠና መስጠት የሚሉት ናቸው፡፡ በተጨማሪም ለጥራት ስርዓት ሰርተፊኬሽን አገልግሎት የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ማነጋገር መልካም ነው፡፡
#ድርጅታችን በንቅናቄው ቆይታ ተቋማት በድርጅታቸው ውስጥ የጥራት ቁጥጥር ሙያተኛ እንዲኖራቸው የሚፈልጉ ከሆነ ሙያተኛውን በደብዳቤ ከላኩ በአንድ ሙሉ ቀን ስልጠና ብቻ አብቅቶ ለስራ መደቡ ዝግጁ አድርጎ የሚልክ ሲሆን በተጨማሪ ቀጣይነት ያለው የማማከር አገልግሎት ስልጠናና ድጋፍ የምናገለግላችሁ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ለስልጠና የምትልኳቸው ሙያተኞች ካሉ ብዛቱ ያልተገደበ ሆኖ የመላኪያ ጊዜ እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ብቻ ነው፡፡
#የጥራት ስራ አመራር ቡድን በተቋም ውስጥ መኖር ለተቋማት ስኬት መሰረት ነው!

        #ድርጅታችን ለአዲስ አበባ ዋና ቢሮ ስራዎች ብቁ የሆኑ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።  #በዚሁ መሰረት ስራ ፈላጊዎች መረጃውን በጥንቃቄ በማንበብ የተጠየቁትን አሟልታችሁ...
20/08/2026



#ድርጅታችን ለአዲስ አበባ ዋና ቢሮ ስራዎች ብቁ የሆኑ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
#በዚሁ መሰረት ስራ ፈላጊዎች መረጃውን በጥንቃቄ በማንበብ የተጠየቁትን አሟልታችሁ እንድታመለክቱ እናሳውቃለን።
#በማስታወቂያ የገለፅነው መሀከል የሚቀነስ ወይም ተፈፃሚ የማይሆን የለምና በጥንቃቄ አንብባችሁ አመልክቱ።

     #በክልል ላሉ ተጨማሪ ስራዎችና ያልተሟሉ መስኮች የወጣ የስራ ማስታወቂያ።  #ባለፈው በወጣው ማስታወቂያ በየከተማው ብቁ የሆኑት ስልጠና ጭምር ወስደው ወደ ስራ ተሰማርተዋል። #ማስታወ...
20/08/2026


#በክልል ላሉ ተጨማሪ ስራዎችና ያልተሟሉ መስኮች የወጣ የስራ ማስታወቂያ።
#ባለፈው በወጣው ማስታወቂያ በየከተማው ብቁ የሆኑት ስልጠና ጭምር ወስደው ወደ ስራ ተሰማርተዋል።
#ማስታወቂያው በግልፅ ተፅፏል። አንብቡ አመልክቱ።
የሚያስደውል ጉዳይ ባለመኖሩ አትደውሉ።
ካለፋችሁ እኛ እንደውላለን ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ገፃችን መልእክት እናስተላልፋለን።
#ቅጥርን አስመልክቶ ለየወቅቱ አመልካቾች የሚተላለፈውን መልእክቶቹን መሰረት በማድረግ ተከታትሉ የታዘዙትን የቅጥር ስርአቶች አሟልቶ ለቅጥር መብቃት ከዘመናዊና ብቁ ስራ ፈላጊ የሚጠበቅ ተግባር ነው።
#ለምዘና ስራ የኮምፒውተር ፅሑፍ ችሎታ የሌላቸው ማመልከት አይችሉም።
https://t.me/worldclassqualityawardethiopia

11/08/2026

10/08/2026

Address

Djibouti Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when World Class Quality Award Organization posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to World Class Quality Award Organization:

Shortcuts

Share